Your channel viewers will see links here, including "subscribe" and "add as friend".
Profile
Name
Muluneh Kegnu Ministries
Description
👉welcome to MULUNEH KEGNU
YouTube channel
👉ወደ Muluneh Kegnu የዩቲዩብ ቻናል እንኳን በደህና
መጣችሁ!
👉የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ እኔ ወንድማችሁ ሙሉነህ ቃኘው
(Muluneh Kegnu) ነኝ።
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መዝሙሮች፣ ስብከቶችና አስተማሪ ትምህርቶች ስለማቀርብ፣ ቻናሉን #Subscribe 👉Like 👉Comment በማድረግ የአገልግሎቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ።
ጌታ ይባርካችሁ!
YouTube channel
👉ወደ Muluneh Kegnu የዩቲዩብ ቻናል እንኳን በደህና
መጣችሁ!
👉የተከበራችሁና የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ እኔ ወንድማችሁ ሙሉነህ ቃኘው
(Muluneh Kegnu) ነኝ።
በዚህ ቻናል መንፈሳዊ መዝሙሮች፣ ስብከቶችና አስተማሪ ትምህርቶች ስለማቀርብ፣ ቻናሉን #Subscribe 👉Like 👉Comment በማድረግ የአገልግሎቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ።
ጌታ ይባርካችሁ!
Subscribers
1.1K
Subscriptions
Recent Activity
|
Muluneh Kegnu Ministries
ትህትና ማለት ምንድን ነው?
ትህትና ማለት ራስን ከሌሎች በላይ አለማድረግ፣ ሌሎችን ማክበር፣ ለማወቅ ፈቃደኛ መሆን እና በትሕትና ማገልገል ነው።
ትህትና ማለት ደካማ መሆን ወይም ራስን አለማክበር አይደለም። ሰው ችሎታውንና የሚያውቀውን እያወቀ፣ ከሌሎች ለመማር ፈቃደኛ መሆኑ ነው።
1. ትህትና በመጽሐፍ ቅዱስ
“በትሕትና እያንዳንዱ ሌላውን ከራሱ እንዲልቅ ይቁጠር።”
— ፊልጵስዩስ 2፥3
ኢየሱስ ክርስቶስ የትህትና ታላቅ ምሳሌ ነው። እርሱ ጌታ ሆኖ ሳለ አገልጋይ ሆኖ አገለገለ። ይህም እውነተኛ ታላቅነት በኩራት ሳይሆን በትህትናና በአገልግሎት እንደሚገለጥ ያስተምረናል።
2.ትሁት ሰው የሚታወቅባቸው 5 ባህሪያት
ሌሎችን ያከብራል። ሰዎችን በሀብታቸው፣ በዕውቀታቸው ወይም በማዕረጋቸው አይመዝንም።
ስህተቱን ይቀበላል። “ተሳስቻለሁ፣ ይቅርታ” ለማለት አያፍርም።
ለሌሎች ይማራል። ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ አያስብም።
ያለ ትዕቢት ያገለግላል። ለሰዎች የሚያደርገውን መልካም ነገር ለማስመሰገን አይሠራም።
ራሱን ያውቃል። ጥንካሬውንም ድክመቱንም በትክክል ይረዳል።
3. ትህትናና ትዕቢት ያላቸው ልዩነት
ትህትና ትዕቢት
ከሌሎች ይማራል። ሌሎችን ያንቋሽሻል።
ስህተቱን ይቀበላል። ሁልጊዜ ራሱን ትክክል ያደርጋል።
ሌሎችን ያከብራል። ሌሎችን ይንቃል።
በተግባር ያገለግላል። ለራሱ ክብር ይፈልጋል።
4. የመጨረሻ መንፈሳዊ መልዕክት
ወዳጄ፣ ትህትና ማለት ራስህን ዝቅ አድርገህ እንድትኖር ሳይሆን፣ ሌሎችን ሳትንቅ በእውነት እንድትኖር ነው። ሰዎች በታላቅ ንግግርህ ሊደነቁ ይችላሉ፤ በትህትናህ ግን ልባቸውን ልትነካ ትችላለህ።
አስታውስ፦ ትዕቢት ሰውን ከሰዎች ያርቃል፤ ትህትና ግን ወደ ሰዎች ያቀርባል።
“እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።” — ያዕቆብ 4፥6
Muluneh Digital Ministries
|
||
|
Muluneh Kegnu Ministries
Muluneh Digital Ministries
እምነት • እውነት • ለውጥ
#MulunehDigitalMinistries #መንፈሳዊምክር #የእግዚአብሔርቃል #AmharicChristian #YouTubeShorts
|
||
|
Muluneh Kegnu Ministries
#ክፍል 13: #በመሞት_ላይ_ያለ
#መንፈሳዊነት_ምልክቶች
ባለፉት 12 ክፍሎች በትንሿ ኢስያ ለነበሩ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ከክርስቶስ ዘንድ የተላከላቸውን መልዕክቶች በዝርዝር ስንማር ቆይተናል። ለሰባቱ ቤተክርስቲያናት ከተላኩ መልዕክቶች አንዳንድ ሀሳቦችን እያነሳ ዛሬ በመሞት ላይ ያለ መንፈሳዊነት ምልክቶችን በጥቂቱ እንማራለን። እንደ አማኝ አለሁ እያልን እየሞትን እንዳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ራሳችንን ማየት አለብን።
#ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን በተላከው መልዕክት፦ "#ሥራህን_አውቃለሁ_ሕያው_እንደ_መሆንህ_ስም_አለህ_ሞተህማል" ይላል። ራእይ 3፥1
#በመሞት_ላይ_ያለ_መንፈሳዊነት_ምልክቶች
1. #አለመፀለይ
አለመፀለይ እየሞተ ያለ መንፈሳዊነት አንዱ ትልቁ ምልክት ነው። አንፀልይም ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት አናደርግም ማለት ነው። ሰው መብላትና መተንፈስ ካቆመ ቀጥሎ የሚገጥመውን መገመት ቀላል ነው። ይሞታል።
ስለ ፀሎት መፅሐፍ ቅዱስ በ1ኛ #ተሰሎንቄ 5፥17-18
"ሳታቋርጡ ጸልዩ በሁሉ አመስግኑ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና" ይለናል።
የሚፀልይ ክርስቲያን በሕይወት የመኖር መንፈሳዊነት አንዱ ማሳያው ነው።
2. #ፍቅርን_መጣል
ፍቅር የአማኞች በሕይወት ላለ መንፈሳዊነታቸው መገለጫ ነው። በአማኝ ሕይወት ፍቅር ከወደቀ መንፈሳዊነት አብሮ ይወድቃል። ፍቅርን መጣል የኤፌሶን ቤተክርስቲያንን እንድትነቀፍ አድርጓታል።
#ራእይ 2፥4
"ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና" ይላል።
በዚህ ብቻ አያቆምም #ንስሃ_ግባ ይለዋል። በዚያ ብቻ አይተውም ንስሐ ባትገባ ብሎ ያስጠነቅቃል። "#መቅረዝህን_ከስፍራው_እወስድብሃለሁ" ይለዋል።
#ራእይ 2፥5
"#እንግዲህ_ከወዴት_እንደ_ወደቅህ_አስብ_ንስሐም_ግባ_የቀደመውንም_ሥራህን_አድርግ፤ #አለዚያ_እመጣብሃለሁ:: #ንስሐም_ባትገባ_መቅረዝህን_ከስፍራው_እወስዳለሁ" ብሎታል።
3. #ቃሉን_ቸል_ማለት
የእግዚአብሔር ቃል ለአማኝ ምግብና መጠጡ ነው። ጤናማ አመጋገብ ጤናን እንደሚጠብቅ ሁሉ፤ ጤናማ መንፈሳዊነት እንዲኖረን የእግዚአብሔርን ቃል ሁልጊዜ መመገብ አለብን።
#1ኛ ጴጥሮስ 2፥3
"ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ" ይለናል።
4. #የኃጢአት_ልምምድ
በኃጢአት ልምምድ ውስጥ መቆየት በመሞት ላይ ያለ መንፈሳዊነት አንዱ ማሳያ ነው። ኃጢአት በሕይወት ላለ መንፈሳዊነት ጠላት ነው። የኃጢአት ድግግሞሽ በሕይወታችን ከተስተዋለ ቶሎ ነቅተን ማቆም አለብን።
#ራእይ 2፥22
#እነሆ_በአልጋ_ላይ_እጥላታለሁ፤ #ከእርስዋም_ጋር_የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ #ንስሐ_ባይገቡ_በታላቅ_መከራ_እጥላቸዋለሁ" ይለናል።
5. #የመንፈስ_ግለት_ማጣት
አማኝ በፀሎት በቃለ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀጣጠል ዘወትር ሕይወቱን መምራት አለበት። መፅሐፍ እንዲህ ይላል::
#ሮሜ 12፥11
"ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ ለጌታ ተገዙ" ይለናል።
የቀደመውን መንፈሳዊ ግለታችሁን አትጡ። እሱን ማጣት እንደ ሎዶቅያ ከእግዚአብሔር የተተፋን እንድንሆን ያደርገናል።
#ራእይ 3:15_16
¹⁵ በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር።
¹⁶ እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
6. #ኑሮ_የሌለው_ክርስትና
አሁን ያለንበት ዘመን አብዛኛዎቹ አማኞች ለመልክ ክርስትና ብቻ ሲጨናነቁ የሚስተዋልበት ጊዜ ነው። የመልክ ወይም የመምሰል መንፈሳዊነትን መለማመድ በኑሮ ወይም በሥራ የታጀበ ኃይል ያለው መንፈሳዊነት እንዳይኖረን ያደርጋል። መንፈሳዊነትን በኑሮ እየገለጥንና መንፈሳዊ ፍሬ እያፈራን የማንኖር ከሆነ እየሞትን መሆናችንን መረዳት አለብን።
#2_ጢሞቴዎስ 3፥5
"የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ" ይለዋል።
7. #የልብ_ድንዳኔ
ይቅር ለማለት የሚታዘዝ መንፈሳዊነት ማጣት። ንስሐ ለመግባት የሚታዘዝ ልብ ማጣ እየሞተ ያለ መንፈሳዊነት ሌላኛው ምልክት ነው።
መፅሐፍ ግን በአጭር ቃል እንዲህ ይላል #ዕብራውያን 3፥15
"ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" ይላል።
#የልብ_እልከኝነት የእስራኤልን ህዝብ በምድረበዳ የፈጀ አደገኛ አጥፊ ነገር ነው።
8. #የመንፈስ_ፍሬ_አለመታየት
የመንፈስ ፍሬ በሕይወት ላለ መንፈሳዊነት አንዱ ማሳያ ነው።
የመንፈስ ፍሬ አይታይብንም ማለት አንድም መንፈሳዊ አይደለንም ወይ አልዳንም ወይ ከመንፈሳዊነታችን እየሞትን ነው ማለት ነው።
#ገላትያ 5፥22
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
#ማጠቃለያ
🎤ለአማኝ ፍቅር መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ ደስታ መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ ሠላም መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ ትዕግስት መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ ቸርነት መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ በጎነት መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ ታማኝነት መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ የዋህነት መንፈሳዊነቱ ነው።
🎤ለአማኝ ራስን መግዛት መንፈሳዊነቱ ነው።
#የወንጌል_አማኞችና_አገልጋዮች _ሆይ_ንቁ !!!
#በመሞት_ላይ_ያለውን_መንፈሳዊነት_አድኑ !!
#መንፈስ_ለአብያተ_ክርስቲያናት_የሚለውን
#ጆሮ_ያለው_ይስማ። #ራዕይ 3:13
|
||
|
Muluneh Kegnu Ministries
በተሰረቀ ልብ ላይ የተተከለው ዛፍ
2ኛ ሳሙኤል 15፥6
እንዲሁም አቤሴሎም ከንጉሥ ፍርድ ሊሰማ ከእስራኤል ዘንድ በሚመጣ ሁሉ ያደርግ ነበር፤ አቤሴሎምም የእስራኤልን ሰዎች ልብ ሰረቀ።
በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ እጅግ አስደንጋጭ ከሆኑ የክህደት መገለጫዎች አንዱ መልክአ ምድሩ የትህትና ማልያ የለበሰ አርቆ ተናጋሪ የሚመስል ነገር ግን በስውር የሰውን ልብ ከእግዚአብሔር አገልጋዮች ነጥሎ ወደ ራሱ የማዞር አደገኛ መረብ የሚዘረጋ አካሄድ ነው።
ይህ የአቤሴሎም አካሄድ የሚበቅለው በለመለመ የእምነት መሬት ላይ ሳይሆን በሰዎች ቅሬታ እና ድክመት አፈር ላይ ነው።
የዚህ መርዛማ ዛፍ ሥር የሚሰደደው የተጎዳ አእምሮን እና የተማረረ ልብን እንደ ማገዶ በመጠቀም ነው።
ይሄ የአቢሴሎም 🌲 ዛፍ በሃገር በቤተክርስትያን በህብረት መሃል ተተክሎ ይታያል ይህ ይህ የአቤሰሎም ዛፍ የሚታይ ምልክትን የያዘ ነገር ግን የማይታይ ሞትን የተሸከመ ነው ።
የሽንገላ ጥላውም በበሩ ቆሞ ጉዳይህ ትክክል ነው ነገር ግን መሪዎቹ አያስተውሉልህም የሚል እኔ ብሆን በዛ ቦታ ያለውት የሚል አደገኛ የውሸት የርህራሄ መረብን መዘርጋት።
የተሰጠውን አደራ ለወንጌል አደራነት ሳይሆን ለግል ታዋቂነት ለዝና እራስ ለመገንባት መጠቀም ሕዝቡን ወደእግዚያብሔር ሳይሆን ወደራስ ማስጠጋት የግል ሰራዊት ስብስብ ማከማቸት አንዱን ጥሎ አጠልሽቶ የራስን ሃሳብ መገንባት እነዚህ ዋና አላማዎቹ ናቸው
የዚህ ዛፍ ግርማ ሞገስ የቱንም ያህል ግዙፍ ቢመስል ፍጻሜው ግን አስደንጋጭ እና አሳማኝ በሆነ መለኮታዊ እውነት ይገለጣል ዛፉ ይረግፋል።
በውሸት እና በግል ውዳሴ ላይ የተገነባው ይህ ግንድ ውስጡ ስለተበላሸ የመጀመሪያው መለኮታዊ ነፋስ ሲመታ በራሱ ክብደት ይፈራርሳል።
ታሪኩ እንደሚያስተምረን አቤሴሎም በረዥም ጸጉሩ በዛፍ መካከል ተንጠልጥሎ እንደቀረ ሁሉ በሰዎች ማጭበርበር ራሱን ከፍ ያደረገ አካል ፈጣሪ ሲያወርደው ውድቀቱ ድንገተኛ እና አሳዛኝ ይሆናል ሃሳቡ ከግብ ሳይደርስ እንደፀጉሩ ተንጠልጥሎ ይቀራል።
የሰውን ልብ የሰረቁ እጆች ባዶ ይቀራሉ የክህደታቸውም ፍሬ በመለኮታዊ ብርሃን ፊት ተቃጥሎ ይጠፋል።
በመሠረቱ የጠቆረ ማንኛውም የስልጣን ግንብ በመጨረሻ በራሱ እሳት ይበላል።
በሰው እንባና ቅሬታ ላይ የተተከለ ዙፋን መሠረቱ አመድ ነውና ነፋስ ሲነካው ተበትኖ ይቀራል የሰውን ልብ በሽንገላ የሰረቀ እጅ ግን የዕለቱ ፍርድ ሲደርስ ባዶነቱ ለትውልድ መሳቂያ ሆኖ ይቀራል።
የሰው ልብ የእግዚአብሔር መቅደስ ነው። በለስላሳ ቃልና በግብዝነት ማልያ ተሸፍኖ የሚመጣን ማንኛውንም የአቤሴሎም መንፈስ በጊዜ መረዳት ከውድቀት የሚታደግ መለኮታዊ ጥበብ ነው።
እውነት ጊዜያዊ ስቃይ ቢኖረውም የክህደት ዛፍ ግን በራሱ መርዝ ተጠምቆ መውደቁ አይቀሬ ነው።
የሌሎችን ስባሪ ልብ ሰብስቦ የራሱ መከለያ ለማድረግ የሚሞክር ሁሉ የራሱ ግንድ በዕለቱ ዐውሎ ነፋስ ሲሰበር ማየት ታሪካዊ እጣ ፈንታው ነው
አቢሴሎሞች የተከሉት ዛፍ በመጨረሻም አድጎ እና ሰፍቶ ብዙ የጥፋት ቅርንጫፍ አውጥቶባቸው እራሳቸውን አንጠልጥሎ ይገድላቸዋል
ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ።
እንደዚህ አይነት ሰዎች ሃሳባቸው ከግብ ሳይደርስ በሰማይ እና በምድር መሃል ተንጠልጥሎ ይቀራል
2ኛ ሳሙኤል 18፥9
አቤሴሎም ከዳዊት ባሪያዎች ጋር በድንገት ተገናኘ፤ አቤሴሎምም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር፥ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ፥ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ፥ ተቀምጦበትም የነበረ በቅሎ አለፈ።
|
||
Friends
Channel Comments
|
Agape4475
(7 months ago)
በርታ
|
|
Almitube-21
(4 months ago)
በርታ ወንድምነት
|
|
mahodatta_vlog
(6 months ago)
Excellent
|
|
ShafirNerson
(6 months ago)
Very nice
|
|
كريمةياسين-خ2ه
(4 months ago)
ሰለም
|
|
towfiqchannal1782-h1u
(4 months ago)
ሙሉነህ በርታልኝ
|
|
Mahadr21
(6 months ago)
በረታ
|
|
ዜደ-ተ7ኈ21
(7 months ago)
ዋውውውው ደስይላል በርታ
|
|
Maki_youTube24
(7 months ago)
በርትዕ ወንድሜ
|
|
ኢብራህምm2
(6 months ago)
ዎው አርፍ ነው ባርታ ዋንድሜ
|
|
ቤተፅጌ21
(7 months ago)
ፀጋውን ያብዛልህ ወንድም አለም በርታልን
|
|
Devide72-y3o
(7 months ago)
ሃይ ሙሌ ተባረክ
|
|
Betiቢቲ
(6 months ago)
ሰለም ዎድሜ
|
|
HayatHayat-t9b
(6 months ago)
ማሻአላህበርታ
|
|
ፋጡማአሰፍ
(4 months ago)
ሰላም ጤና ተመኝሁ ወንድም በርታ አይዞህ
|
|
HdiyaShifa
(6 months ago)
ሙሉዬ በርታ
|
|
ፅናትአለም
(7 months ago)
ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ
|
|
ቢቲ2
(7 months ago)
በረታልኝ በጠም ጥሩ ትምርትናዉ
|
|
ስዴትመምህሬ
(7 months ago)
ሰላምህይብዛልህ
|
|
Hewat-c4k
(7 months ago)
Berta wandeme
|
Add comment







































